Search

Thursday, 7 November 2019



👉 ቶሎ-ቶሎ መረጃዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ LIKE & SHARE ማረጉን አይርሱ!
የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ



ሳተላይትን ለመቀበል የሚያስችል መሠረታዊ የሳተላይት መሳሪያ ሲሆን በጥሩ ሁኔታ እንዲሰራ ከተፈለገ ትክክለኛ በሆነ (accurate ​) ዲግሪ (angle​) ሊስተካከል ይገባዋል።


እያንዳንዱ የዲሽ ዲግሪ በነጥብ ሳይቀር የራሱ ሳተላይት አለው። ለምሳሌ፦ MBC እና EBS ያሉበት ሳተላይት ይለያያል። EBS ​ 8W​ ሲሆን MBC ደግሞ 7.3 W​ ነው ። በመካከላቸው ያለው የአንግል ልዩነት 0.7 ሲሆን አንዳንዴ EBS በጥራት እየሠራ ሌሎቹ ቻናሎች ሙሉ ለሙሉ ይጠፋሉ አልያም ጥራታቸው ሲጓደል እናያለን ። ሆኖም ሁለቱ ተመጣጥነው እንዲሰሩ ስለሚደረግ በጥራት ልናይ ችለናል። ይህ ችግር የሳተላይት ሽፋናቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ሳተላይቶች ደግሞ የበለጠ ፈታኝ ይሆናል፡፡

___________________

ከዚህ በተጨማሪ ግን ዲሻችን በየጊዜው እንዲስተካከል የሚያደርጉ ዋና ዋና ችግሮች የሚከተሉት ናቸው።
___________________



የዲሽ መጠን ማነስ
የዲሽ መጠን ሲያንስ የመሳብ መጠንም ይቀንሳል ሆኖም ሀገራችን ውስጥ ለምሳሌ ናይልሳት ያለው ሽፋን ከፍተኛ ስለሆነ ባለ60ሳሜ ዲሾችን ልንጠቀም እንችላለን።



የዲሽ ብሎኖች ስፓናቶ መሆን
በተደጋጋሚ በሚፈጠር ብልሽት ምክንያት ብሎኖች ሲታሰሩና ሲፈቱ ለዚህ የመላላት ችግር ይጋለጣሉ።



የLNB መድከም
ከተሰራበት ፋብሪካ አልያም ብዙ ጊዜ ከማገልገሉ የተነሳ የሚፈለገውን quality​ ያለመስጠት ችግር።



የዲሽ ገመድ (cable​) መቆራረጥ
ገመድ በተቆራረጠ ቁጥር strength​ ይቀንሳል። ካልተቻለ ከሁለት ጊዜ በላይ ባይቀጠል መልካም ነው። ከዚህ በተጨማሪ ለዝገትም ያጋልጣቸዋል።



የኬብል conector​ አካባቢ ዝገት
የዝናብ ውሀ ስለሚያገኛቸው ለዝገት ይጋለጣሉ ከዛጉ ደግሞ signal አያስተላልፋም።



የዲሽ ማስቀመጫ ጣሪያ ሁኔታ
የዲሽ ማስቀመጫ ጣሪያ በዚህ ስራ ከፍተኛ የሆነ ሚና አለው። ጣሪያ ከስር በርካታ አግዳሚዎች ከሌሉትና የቆርቆሮው ጌጅ ዝቅተኛ ከሆነ በቀላሉ ቦታውን ይለቅቃል።



የአካባቢው በዛፍ (በግንብ) የመሸፈን ሁኔታ
ሳተላይት የሚመጣው አግድም ከሆነ በዛፍም ሆነ በግንብ በቀላሉ የመከለል ችግር ይገጥመዋል። የዲሹ አቅጣጫ ወደ ምዕራብ ከሆነ ዲግሪ እየቀነሰ ሲመጣ እንዲሁም የዲሹ አቅጣጫ ወደ ምስራቅ ከሆነ ዲግሪ እየጨመረ ሲመጣ።



የዲሽ ማስቀመጫ ጣውላ መበስበስ
አብዛኛው ተጠቃሚ የዲሽ ማስቀመጫው ጣውላ ስለሆነ ፀሐይና ዝናብ ሲፈራረቅበት ይከሳል/ ይወፍራል/ ይበሰብሳል።



ማያያዣ ሚስማሮች መልቀቅና መጫወት
ከጊዜ በኋላ ጣውላው ሲከሳ ሚስማሮች እየለቀቁ ሲሄዱ ዲሹ በትንሽ ነፋስ መጫወት ይጀምራል ስክራች ያደርጋል።



የሪሲቨሮች ሁኔታ
ስሪታቸው የቆዩ ሪሲቨሮች በአሁኑ ሰዓት ላሉ ሳተላይቶች ስለማይመጥኑ ቢወገዱ ይሻላል። በተለይ Erostar 555 ፣ 777 እና የመሳሰሉ የሽማግሌዎች ሪሲቨር በርካታ ችግሮች አሉባቸው።



የስዊች መድከም/አለመስራት
Switch ለዝናብ ውሀ ከተጋለጡ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ይበላሻሉ።



የአካባቢው ለነፋስ ያለው ተጋላጭነት
ነፋስ ከፍተኛ የሆነ ግፊት ስላለው የዲሽን አቅጣጫ የማስቀየር አቅም አለው። ስለዚህ qualityው ይወጣል፡፡



የአንዳንድ ሳተላይቶች frequency ደካማ መሆን
የአንዳንድ ሳተላይቶች ፍሪኩየንሲ የማይጨበጥ አይነት ይሆናል፡፡ (ለምሳሌ፦ ናይልሳት ላይ 11096 H እንዲሁም ያህሳት ላይ 12015 H እና 11785 H)



የዲሽ ባለሙያው ክህሎት ችግር
አንዳንድ ባለሙያዎች ለስራው ጀማሪዎች በመሆናቸው ምክንያት በትክክል quality ላይመጣላቸው ይችላል።



የተጠቃሚው ስህተት ናቸው
በተለይ እዚህ ላይ ብዙ ጊዜ የሚስተዋለው ችግር ከሪሲቨሩ ጀርባ የሚሰካውን ኮኔክተር መነካካትና የአሉሚኒየሙን ከቀጫጭን ሽቦዎች ከመዳቡ ወፍራም ሽቦ ጋር ማገናኘት።
ህፃናት menu ውስጥ በመግባት የማይነካኩ settingኦችን የመነካካት ችግሮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡



ምንጭ-በዳኒ ዲሽ የተፃፈ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬



🚩እንደተለመደው ሁሌም አዳዲስ ነገሮች post ሲደረጉ በቶሎ እንዲደርስዎ Facebook ፔጃችን like & share ያድርጉልን፡፡ https://www.facebook.com/dishethio1


♨️ በቴሌግራም የቻናላችን ተከታይ በመሆን በየሰዓቱ የምንፅፋቸውን ነገሮችንም ለመከታተል ከፈለጉ https://t.me/kanadishtechnology ብለው ሊቀላቀሉን ይችላሉ። ወደ ቻናላችን ሲገቡ የሁሉንም HD ሪሲቨሮች ሶፍትዌር በነጻ ያገኛሉ ።

No comments:

Post a Comment